image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በሙስና መከላከል እና እስትራቴጂ ዙሪያ ለዘርፍ ኮሚቴዋችና ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ምክር ቤት ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የካቲት 24/62018, 2017
ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም ሰው ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል አቶ መላኩ ጌታሁን የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ስልጠና ሰጠ ። የካቲት 24/2018 ዓ.ም የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በሙስና መከላከል እና እስትራቴጂ ዙሪያ ለዘርፍ ኮሚቴዋችና ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ምክር ቤት ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። አቶ ስዩም ቲቶ የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት የድጋፍ፣ ክትትል እና ቁጥጥር ቡድን መሪ በሙስና መከላከል እና እስትራቴጂ ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤን በመፍጠር የመንግስት እና ህዝብ ሃብት በአግባቡ ስራ ላይ በማዋል፣ አገልግሎት ከእጅ መንሻ በፀዳ ሁኔታ ለዜጎች እንዲሰጥና ስርቆትን የሚፀየፍ ትውልድ እንዲፈጠር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የልደታ ክ/ከተማ የፀረ ሙስና መከላከያ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መላኩ ጌታሁን እንደተናገሩት ሙስና እና ብልሹ አሰራር ስልቱን እየቀያየረ በመሆኑ ሁሉም አካል ግንዛቤውን በመጨመር ሙስናን ሊያጋልጥ የሚችል የአሰራር ስርዓት በመዘርጋትና በቁርጠኝነት በመከላከል ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው ወቅታዊና የሚያመጣው ውጤትም ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው እራሳችንን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በመጠበቅ በፅኑ መታገል ይኖርብናል በማለት ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች