image
image
image
image
image

ስነ-ምግባራዊ ትውልድን ለመገንባት የሚዲያ ስራዊቱ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

ህዳር 19/3/2018, 2017
ስነ-ምግባራዊ ትውልድን ለመገንባት የሚዲያ ስራዊቱ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ የሚዲያ ሰራዊቱ "ትውልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር " በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ውይይት አካሂዷል።፥ በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት የሚዲያ ሰራዊቱ የግብረ -ገብ እሴቶች በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲሰርፁ በትጋት ልትሰሩ ይገባል ብለው ምክንያቱም የግብረ ገብ እሴቶችን በማስረፅ መልካም ስነ-ምግባርን ከገነባን ሙስና ቦታ አይኖረውም በማለት ገልፀዋል። ሙሰኝነት መነሻው አስተሳሰብ ነው ያሉት አቶ አሰፋ አስተሳሰብ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት ሙስናን ማጥፋት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል። የሚዲያ ሰራዊቱ ማህበረሰቡ ሙስናን እንዲታገል ማንቃት አለበት ያሉት አቶ አሰፋ የሰላም እና የስነ-ምግባር እሴቶችን በማስረፅ ማህበረሰቡን ማንቃት ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ወርቁ እንደተናገሩት የስነ-ምግባር እሴቶችን በማህበረሰቡ ዘንድ በማስረፅና በማንቃት ማህበረሰቡ ሙስናን ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ እንዲዋጋው ማድረግ አለብን ሲሉ ገልፀዋል። ወ/ሮ ሲፈን አክለውም ሙስና የሀገርን ዕድገት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚጎዳ በመሆኑ ተግባር በመሆኑ ተረባርበን ልንታገለው ይገባል ብለው የሚዲያ ሰራዊቱም ማህበረሰቡን በማስገንዘብ ረገድ የመሪነት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። በልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ጀንበሩ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት ሙስና የሀገር ብልፅግናን የሚጎዳ በመሆኑ በጋራ ልንከላከለው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች