image
image
image
image

በሙስና ፅንሰ ሀሳብና መከላከያ መንገዶች የምክር ቤት ሚና

ጥቅምት 15/2/2018, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ስልጠና ሰጠ። ጥቅምት 11/2018 የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት በሙስና ፅንሰ ሀሳብና መከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለጽ/ቤቱ እና ለወረዳ ምክር ቤት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ዋለልኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ እንደተናገሩት ሙስና ከጊዜ ወደ ጊዜ አሰራሩን እየቀያየረና ሰንሰለቱን እያሰፋ በመሆኑ ግንዛቤያችንን በመጨመር ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት በመከላከል ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። ስልጠናውን የሰጡት የልደታ ክ/ከተማ የፀረ ሙስና መከላከያ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መላኩ ጌታሁን እንደተናገሩት የህግ አፈጻጸሙን ተግባራዊ ለማድረግ ተጠርጣሪን እና በሙስና የተያዘን አካል ተጠያቂ ማድረግ ላይ ተስፋ ሳንቆርጥ በመታገል እና ከሙስና የፀዳች ሀገር ለትውልድ ለማሻገር የህብረተሰቡን አመለካከት መቀየር ይኖርብናል በማለት ተናግረዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከስልጠናው ከፍተኛ ግንዛቤ እንዳገኙና ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል አና አራሳቸውን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች