image
image
image
image
image

ከእጅ መንሻ የፀዳ አገልግሎት በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲፈታ እየሰራ መሆኑን የልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን ገለጸ።

ህዳር 4, 2017
የሥነ- ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ምንነትና አስፈላጊነትና አሰራር ዙርያ ለመንግስት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። የክ/ከተማው ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደገለጹት ስልጠናውን መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት በተቋማት ከእጅ መንሻ የፀዳ አገልግሎት ለመስጠትና ሌብነትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በመስራት የመንግሥትና የህዝብ ሀብት እንዳይመዘበር ለማድረግ ነው ብለዋል። ወ/ሮ እማዋይ አክለውም ሙስና በአገልግሎት አሰጣጡም ችግሮች እንዳይኖርና ህዝብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ክትትሎችን ማድረግ ሙስና ከመፈጸሙ በፊት ማስቆምና ችግሮች ሲፈጠሩ የተጠያቂነት ስርዓት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር እንሰራለን ብለዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው ሙስናን ለመከላከል አስፈላጊውን ስራ እንሰራለን ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች