image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ለ21ኛው ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ቀን መታሰቢያነት በትምህርት ቤቶች የግብረ ገብና ፀረ ሙስና ክበባት መካከል ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ

ህዳር 19/3/2018, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ ለ21ኛው ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ቀን መታሰቢያነት በትምህርት ቤቶች የግብረ ገብና ፀረ ሙስና ክበባት መካከል ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ ህዳር 19/2018፣ ልደታ ክፍለ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፣ 21ኛውን ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው ስር በሚገኙ የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግብረ ገብና የፀረ-ሙስና ክበባት መካከል አጓጊ የጥያቄና መልስ ውድድር በድምቀት ተካሄደ። የዕለቱ መልክት "ትውልድን በሥነ ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ት/ት/ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎች፣ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክፍል ቡድን መሪና ባለሙያዎች፣ መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት ነው ውድድሩ የተከናወነው። የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ሙስና በሀገር እድገት ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅእኖ በመገንዘብ፣ ተተኪው ትውልድ ከወዲሁ በስነ-ምግባር የታነጸ እና ለሙስና አሳልፎ የማይሰጥ ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል። በውድድሩ ላይ የተሳተፉት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፀረ-ሙስና ክበባት ተወካዮች፣ በስነ-ምግባር መርሆች፣ በፀረ-ሙስና ህጎች እና በሀገራዊ የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች በብቃት በመመለስ አበረታች ፉክክር አሳይተዋል። በተለይም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያሳዩት የነቃ ተሳትፎ እና ስለ ሙስና አስከፊነት ያላቸው ግንዛቤ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የታዳሚው ምላሽ አረጋግጧል። የልደታ ክፍለ ከተማ አስ/ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት፣ ትምህርት ቤቶች ዕውቀትን ብቻ ሳይሆን መልካም ስነ-ምግባርን የማስረጽ ኃላፊነት አለባቸው። በመሆኑም በክበባት መካከል የሚደረጉ እንዲህ ዓይነት ውድድሮች ተማሪዎች እርስ በርስ እንዲማማሩ እና የፀረ-ሙስና ትግሉን ባለቤትነት ስሜት እንዲላበሱ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳላቸው አስምረውበታል። ውድድሩ በከፍተኛ ፉክክር ተጠናቆ አሸናፊ ለሆኑት የክበብ አባላት የእውቅና የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተበርክቷል። ዘገባው የልደታ ክፍለ ከተማ አስ/ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ነው፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች