ቀን: መስከረም 22/01/2018, 2017

የእለቱ መልዕክት

  • የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል "መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ሙስናን ለመከላከል የሴቶች ሚና" በሚል ርዕስ ለክፍለ ከተማው ሴት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የሴቶች ማህበር ተወካዮች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ እንደተናገሩት ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሀገርን እድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ከሙስናና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ማህበረሰብ ለመገንባት ያላቸው ሚናም የላቀ ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ሴቶች በተፈጥሯቸው ያላቸውን የታማኝነትና የኃላፊነት ስሜት በመጠቀም የለውጥ ሃዋርያ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው በበኩላቸው፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ ሴቶች በሙስና ምክንያት ከሚደርስባቸው ልዩ ጫና ተላቀው፣ የችግሩ ሰለባ ሳይሆኑ የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የመከታተያ ክፍሉ ባለሙያ አቶ መላኩ ጌታሁን በበኩላቸው ሴቶች በቤተሰብ ደረጃ የስነ-ምግባር እሴቶችን በማስተማር፣ በስራ ቦታቸው የህግ የበላይነትን በማስከበር እና ብልሹ አሰራር በማጋለጥ ረገድ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በመከታተያ ክፍሉ ባለሙያ በአቶ አያሌው ብሩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡



      
       የልደታ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል

ዝርዝር መረጃ