image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ህዳር 13/3/2018, 2017
በልደታ ክ/ከተማ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ በክ/ከተማው "ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 21ኛውን የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ባስተላለፍት መልዕክት መንግስት ባለፍት የለውጥ ዓመታት ሙስናን በመከላከል ሂደት በርካታ ስራዎች ሰርቷል ብለው በተለይም ለብልሹ አሰራር የተጋለጡና ተገልጋይ ምሬት ሲያሰማባቸው የነበሩ ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ በአሰራርና በአደረጃጀት እንዲዘመኑ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የማማድረግ ስራ ሰርቷል ሲሉ ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም ሙስና የዜጎችን በተለይም የወጣቶችንና ሴቶችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ወጣቶች በስነ-ምግባር ታንፃቹህ እና መንግስት ሙስናን ለመከላከል የዘረጋውን የአሰራር ስርዓት ተጠቅማቹህ መታገል ይኖርባቹሀል ሲሉ ተናግረዋል። ሙስናን መቅረፍ የሚቻለው የመከላከል ስራው ህዝባዊ መሰረት ሲኖረው በመሆኑ እንደ አስተዳደር ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይቶች እያደረግን ግብዓቶችን እየወሰድን ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ሙስናን በመከላከል ሂደት ሁላችንም በጋራ መቆም አለብን በማለት ገልፀዋል። እንደ መንግስት የብልፅና ጉዞው እውን የሚሆነው በርካታውን የማህበረሰብ ክፍል የሚሸፍነውን ወጣቱን ተጠቃሚነት ማድረግ ሲቻል ነው የሚል እምነት ተይዞ ወጣቱ አቅሙንና ተሳትፎውን እንዲያሳድግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ተጠቃሚነትቱ እየተረጋገጠ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች