image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

ሰኔ 1, 2018
"ሙስናና ብልሹ አሠራርን መታገል ቀጣይነት ያለው ተቋማዊና ሕዝባዊ ንቅናቄን ይጠይቃል!" የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ከክፍለ ከተማው ስር ከሚገኙ የወረዳ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል ። የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው ሲሆኑ፣ በንግግራቸውም ሙስናና ብልሹ አሠራርን መታገል የአንድ ወቅት ተግባር ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ሂደት መሆኑን አብራርተዋል ። አክለውም ክፍሉ በተለይም በሥነ-ምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል ጥናትና በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራዎች ላይ እጅግ አበረታችና ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል ። በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች የአመራሩ ቁርጠኝነትና የባለሙያዎች ተነሳሽነት ውጤት መሆናቸውን ገልጸው፣ የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል ። የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያ የሆኑት አቶ መላኩ ጌታሁን አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ዋና ዋና ተለይተው የቀረቡ ሲሆን፡- የአቅም ግንባታ ስራዎች በክፍለ ከተማ ደረጃ ለ1,839 አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለ3,632 አመራሮችና ባለሙያዎች በሥነ-ምግባር፣ በሙስና ወንጀል መከላከልና በሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ሰፊ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል ። ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን ፣ በ22ኛው ዓለም አቀፍና 21ኛው ሀገራዊ የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር ላይ በክፍለ ከተማ ደረጃ 23,186 የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ትልቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተፈጥሯል ። በትምህርት ተቋማት በግብረ ገብና ፀረ ሙስና ክበባት በማቋቋም በትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ላይ ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል ። ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሠራር ስርዓት በማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር የትስስር ሰነድ በመፈራረም የተቀናጀ የሥራ ግንኙነት ተፈጥሯል ። በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሊባክን የነበረውን የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ 454,825 ብር ማዳን ተችሏል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ያጋጠሙ ጥቂት ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ለቀጣይ የሥራ ዘመን ይበልጥ በቁርጠኝነት ለመሥራትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች