image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል ከሲቪክ ማህበራት ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ

ህዳር 14, 2018
የፓናል ውይይቱ በዓለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ነው የተካሄደው። በልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን መሪ ወ/ሮ እማዋይ አበባው እንደተናገሩት ሲቪክ ማህበራት ሙስናን በመከላከል ረገድ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለው ሙስና የሀገር ልማትና ዕድገትን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ በጋራ መታገል ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል። ሙስናን መታገል የሁሉንም ዜጋ ርብርብ የሚጠይቅ በመህኑ ሁሉም ዜጋ ርብርብ ማድረግ አለበት ብለዋል ወ/ሮ እማዋይ። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስናን ለማጥፋት በትኩረት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል። የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክፍል ባለሙያ የሆኑት አቶ አያሌው የመወያያ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች