image
image
image
image
image

በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባትና ብልሹ አሰራርን ለመታገል በ2018 በጀት አመት በመቀናጀና በተደራጀ አግባብ ከፍተኛ ስራዎች መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

መስከረም 18, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ ውይይት አደረገ። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ‎የክፍለ ከተማው የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ(ተወካይ) አቶ አያሌው ብሩ እንደገለፁት የተያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ለማስፈፀም በጀት ዓመት ከፍተኛ ስራዎች መስራት እንደሚገባ ገልፀው በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት በትምህርት ቤቶች ስልጠናዎችን መስጠትና የስና ምግባርና ፀረ ሙስና ክበባትን ማጠናከር እንዲሁም የሙስና መከላከልና ብልሹ አሰራርን ለመታገል ጥቆማዎችን በመቀበል፣በመለየትና መረጃን በማደራጀት እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ በሚያስችል አግባብ መስራት እንደ ሚገባ ገልጸዋል ። በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው ስርአት ለማስፈን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር በ2018 በጀት አመት በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አያሌው ገልፀዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በ2018 በጀት አመት የተያዘውን እቅድ መወያየት መቻላችን በጋራ ለመስራትና ከብልሹ የአራር የፀዳ ትውልድን መገንባት እንደሚያስችል ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች