Welcome to Lideta Subcity Ethics and Anti-Corruption Division!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በሰላም መጡ!       ራዕያችን በ2025 ሙስና ለከተማ አስተዳደሩ ልማትና መልካም አስተዳደር ግቦች እንቅፋት ከማይሆንበት ደረጃ ማድረስ ነው፡፡

የልደታ የስነ-ምግባርና
ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል

የልደታ የስነ-ምግባርና
ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል

የልደታ የስነ-ምግባርና
ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል

የመከታተያ ክፍሉ ቡድን መሪ መልእክት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል በክፍለ ከተማው ባሉ መንግስታዊ ተቋማት የግልፅነት እና ተጠያቂነትን ሥርዓት ለማጠናከር በወሰደው የቅንጅታዊ አሰራር የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማፋጠን ፋይዳው የጎላ ተግባር መሆኑን ይገልፃል። ይህ ጅምር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመንግስት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ የማህበረሰብ መሪዎች እና ነዋሪዎች ጋር በመተባበር እየተካሄደ ነው።

መከታተያ ክፍሉ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ውስጥ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመለየት፣ በመከላከል እና በመቅረፍ ግብአቶች ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ እማዋይ አበባዉ , የልደታ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ቡ/መሪ
image description

በመከታተያ ክፍሉ የሚከናወኑ
ዋና ዋና ተግባራት

በልደታ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት:-

በዝርዝር ይመልከቱ

የልደታ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል

ዉድ ደንበኞቻችን በሀገራችን ሙስና ስር የሰደደና የዜጎችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መብቶችን የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ ዜጎች በሀገራቸዉ መብታቸዉን በአግባቡ እንዲይጠቀሙ ጫና ሲፈጥር የቆየ በሽታ ነዉ፡፡ መንግስትም ይህንኑ በመገንዘብ ችግሩን በአስቸኳይ ለመፍታት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ዉጤቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በስነ- ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ላይ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍሉ ሙስናን ለመከላከል ከሚከተላቸው ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የሙስና መከላከል ስራን ውጤታማነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ በጠንካራ እሴት ሊይ የተገነቡ ዜጎች በአቋራጭ የመበልጸግ ፍላጎት የላቸውም ፤ ስርዓት አልበኝነትን ይቃወማሉ፤ ውሳኔያቸው በስሜት ሳይሆን በምክንያት ነው፤ አገልግሎት በሚሰጡባቸው ተቋማት ወይም በተሰማሩበት የስራ መስክ በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው ህዝባቸውን ያገለግላሉ፣ ሙስናንም ይጠየፋሉ፡፡ በዚህም ሰላም እንዲሰፍን፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ይህን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከመከታተያ ክፍሉ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡

ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!

የመከታተያ ክፍሉ ባለሙያዎች

አቶ አያሌዉ ብሩ

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ

አቶ መላኩ ጌታነህ

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ

አቶ ሲራክ አድነዉ

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ

ወ/ሮ ድንቅነሽ ጣፋ

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያ